በህንድ በአንድ ቀን 6 ሺህ 148 ሰዎች በኮቪድ-19 ህይወታቸው አለፈ

ሰኔ 3/2013 (ዋልታ) – በህንድ በአንድ ቀን ብቻ በኮቪድ-19 ምክንያት የ6 ሺህ 148 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል፡፡

በህንድ ወረርሽኙ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ይህ ከፍተኛ ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

አገሪቱ በአሁኑ ሰዓት በተከታታይ ለሦስት ቀናት ያህል በየቀኑ ከ 100 ሺህ ያላነሱ አዳዲስ በኮቪድ የተያዙ ሰዎች ማስመዝገቧንም ተነስቷል፡፡

በአጠቃላይ በአገሪቱ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 29.1 ሚሊዮን የተሻገረ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 359 ሺህ 676 መድረሱ የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ህንድ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ለዜጎቿ  ከሰጠችው 3.4 ሚሊዮን ጨምሮ በአጠቃላይ ለ242.7 ሚሊዮን ክትባት መስጠቷን ሚኒስቴሩ አክሏል፡፡

ህንድ ከአሜሪካ ቀጥሎ በዓለም እጅግ ከፍተኛ ቁጥር በኮቪድ የተያዙ ሰዎች ያሉባት አገር ናት።

በአገሪቱ የቫይረሱ አሳሳቢነት እየጨመረ ሲሆን በርካታ ዜጎቿን በወረርሽኙ በማጣት ከአሜሪካ በመቀጠል በሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ አናዶሉን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡