በማድሪድ የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

የካቲት 18 /2013 (ዋልታ) – በስፔን ማድሪድ በተካሄደ የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡

በሴቶች የ3 ሺህ ሜትር አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ 8 ደቂቃ ከ22 ሰከንድ ከ65 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት አሸናፊ ሆናለች፡፡

ሌላዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ለምለም ሃይሉ እና ኬንያዊቷ ቢትሪስ ቺቤት 2ኛ እና 3ኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል፡፡

በ800 ሜትር አትሌት ሃብታም አለሙ 1 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ ከ94 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት አሸናፊ ሆናለች፡፡

በወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር ደግሞ አትሌት ሰለሞን ባረጋ ርቀቱን 3 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ ከ42 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት አሸንፏል፡፡

በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር ደግሞ ሂሩት መርሻ 4 ደቂቃ ከ9 ከ42 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ርቀቱን በአሸናፊነት አጠናቃለች፡፡

(ምንጭ ፡- አትሌቲክስ ፌዴሬሽን)