በምርጫ ህጉ መሰረት ውጤት ይፋ እስከሚደረግ ድረስ መራጮች በትግስት እንዲጠባበቁ ቦርዱ አሳሰበ

ሰኔ 15/2013 (ዋልታ) – በምርጫ ህጉ መሰረት ውጤት በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል ይፋ እስከሚደረግ ድረስ መራጮች በትግስት እንዲጠባበቁ ቦርዱ አሳሰበ።

ቦርዱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ “ውድ መራጮች በትላንትናው እለት ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም በከፍተኛ ንቃትና ትእግስት ድምጻችሁን ስለሰጣችሁ እያመሰገንን፤ በምርጫ ህጉ መሰረት ውጤት በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ እስከሚሆን ድረስ በትግስት እንድትጠባበቁ እና ከሌሎች ማንኛውንም ምንጮች የሚወጡ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንድትቆጠቡ ስንል ልናሳውቅ እንወዳለን” ሲል መልእክቱን አስተላልፏል፡፡