በሴካፋ ውድድር ኢትዮጵያ እና ብሩንዲ አንድ አቻ ተለያዩ

ሐምሌ 16/2013 (ዋልታ) – የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ (ሴካፋ) ከ23 ዓመት በታች የወንዶች እግር ኳስ ውድድር የኢትዮጵያ እና ብሩንዲ ቡድኖች ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቅቋል።
በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተደረገው በዚህ ጨዋታ ቸርነት ጉግሳ ለኢትዮጵያ በ44ኛው ደቂቃ እንዲሁም ለብሩንዲ ሀኪዚማና ኢሳ በ66ኛው ደቂቃ ግብ ማስቆጠራቸውን ከኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡