በሸካ ዞን በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት የተገነባው 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ

ሰኔ 10/2013 (ዋልታ) – በሸካ ዞን በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት የተገነባው የደገሌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመርቋል።

በምረቃ ስነሥርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውን ጨምሮ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ ስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የደገሌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ተገንብተው የተመረቁ ትምህርት ቤቶችን ቁጥር 17 አድርሶታልም ነው የተባለው።

ትምህርት ቤቱ ስምንት የመማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ ሙከራ እና የአስተዳደር ብሎኮችን ያካተተ ሲሆን፣ ለግንባታ 10 ሚሊየን ብር ወጪ መደረጉ ተገልጿል።