በቡድን በመደራጀት የተለያዩ ወንጀሎችን የፈፀሙ 51 ተጠርጣሪዎች ተያዙ

መጋቢት 13/2014 (ዋልታ) በመዲናዋ በቡድን በመደራጀት የተለያዩ ወንጀሎችን የፈፀሙ 51 ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ወንጀል ፈፃሚዎቹ ልዩ ልዩ የመሰረተ ልማት አውታሮችን ኢላማ በማድረግ ወንጀል ሲፈፅሙ እንደነበር ተገልጿል።
በተለይ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር የኃይል ማስተላለፊያ ኬብሎችን፣ የኢትዮ ቴሌኮም ለልዩ ልዩ አገልግሎት የዘረጋቸውን ኬብሎች እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ወንጀሉን ሲፈፅሙ እንደነበርም ተጠቁሟል።
በተጨማሪም ለጋራ መኖሪያ ቤቶች የኤሌትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ የተዘረጉ የኤሌትሪክ መስመሮች ላይ ትኩረት አድርገው ወንጀሉን ሲፈፅሙ እንደነበር በአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዘርፍ የልዩ ልዩ እና የተደራጁ ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር አለማየሁ አያልቄ ገልፀዋል፡፡