በአማራ ክልል የግብርና ምርምር ሥራዎች ተጎበኙ

ጥቅምት 17/2014 (ዋልታ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እያከናወቸው ያሉ የግብርና ምርምር ሥራዎች ተጎበኙ፡፡
ጉብኝቱ በከፍተኛ የትምህርትና የግብርና ምርምር ተቋማት በተውጣጡ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት የተካሄደ ነው፡፡
የአነስተኛ እርሻ ባለቤት የሆኑ አርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ኑሯቸውን ለማሳደግ በምጃር ሸንኮራ ወረዳ መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ተግባራዊ እየተደረጉ ከሚገኙ ፕሮጀክቶች መካከል የፎር አር ኒውትረንት ስትዋርድሺፕ ፕሮጀክት አንዱ ነው፡፡
ፕሮጀክቱ ላለፉት 3 ዓመታት በወረዳው 8 ቀበሌዎች ባቋቋማቸው ሰርቶ ማሳያዎች በማዳበሪያ አጠቃቀም ዙሪያ ለአርሶ አደሮች ተግባር ተኮር ሥልጠናዎችን እየሰጠ ነው፡፡
የፕሮጀክቱ ብሔራዊ አማካሪ ኮሜቴ ሰብሳቢ ሸለመ በየነ (ፕ/ር) ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ ለማዳበሪያ የምታወጣውን የውጭ ምንዛሪ በመቀነስ ያለው ድርሻ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የወረዳው ዋና አሰተዳዳሪ ታደሰ ቦሰት በበኩላችው ፕሮጀክቱ የማዳበሪያ ብክነትን በማስቀረትና የአርሶ አደሩን ምርታማነት በማሳደግ ረገድ ሚናው ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
እንደ ሲዲኤፍ ካናዳ የኮሙዩኒኬሽን ክፍል መረጃ ፕሮጀክቱ ከካናዳ መንግሥትና አጋሮቹ በተገኘ 17 ሚሊዮን የካናዳ ዶላር በኢትዮጵያ፣ ጋናና ሴኔጋል እየተተገበረ ነው፡፡
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!