በአብዬ በሚገኙ ተቀናቃኝ ጎሳዎች መካከል የሰላም ስምምነት ተፈረመ

በአብዬ በሚገኙ ተቀናቃኝ ጎሳዎች መካከል የሰላም ስምምነት

በአብዬ ግዛት የሚገኙ የሚስሪያ እና ዲንካ ጎሳዎች መካከል የሰላም ስምምነት ተፈረመ፡፡

በሚስሪያ በኩል ጃዕሚ አልሲድቅ እንዲሁም በዲንካ ጎሳ በኩል ደግሞ ዋር ሀመዲን ስምምነቱን ተፈራርመዋል፡፡

በአብዬ አሚት በምትባል ከተማ በተካሄደው የሁለቱ ጎሳዎች የጋራ ስብሰባ በአካባቢው በተለያየ ጊዜ ይከሰት የነበረውን ግጭት በማስወገድ በጋራ ሰላምን ለማስፈን ስምምነት ደርሰዋል፡፡

በስምምነቱ አካባቢውን ከተኩስና ወታደራዊ እንቅስቃሴ የፀዳ ለማድረግ፣ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት፣ የድንበር አካባቢ ወንጀሎችን እና ለበርካታ ጊዜያት በግጦሽ ሳርና የመጠጥ ውሃ ምክንያት ይከሰት የነበረውን የእርስ በእርስ ግጭት ለማስቆም የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል ተብሏል፡፡

በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ በተባበሩት መንግሥታት የአብዬ ጊዜያዊ የጸጥታ ሃይል (ዩኒስፋ) የሰሜን ሴክተር ላይዘን ኃላፊ ብርጋዴር ጄኔራል ዋኘው አለሜ እንዲሁም የ23ኛ፣ 24ኛ እና 25ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አዛዦች መገኘታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡