በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ዜጎች ቁጥር 3,000 ደረሰ

መጋቢት 28/2013 (ዋልታ) – በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ዜጎች ቁጥር 3 ሺህ ደርሷል፡፡

በትናንትናው እለት 37 ሰዎች በቫይረሱ ለህልፈት መዳረጋቸውን ተከትሎ የሟቾች ቁጥር 3 ሺህ መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሪፖርቱ እንዳመላከተው ከ9 ሺህ 38 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 2 ሺህ 138 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል፡፡

በሌላ በኩል 1 ሺህ 54 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 163 ሺህ 22 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 217 ሺህ 327 መድረሱም ነው የተገለጸው፡፡