በኢትዮጵያ የእጣንና ሙጫ ደን ከአደጋ ለመታደግ ታዋቂ ሰዎች በጋራ እየሰሩ መሆናቸው ተገለጸ

ሚያዝያ 05/2013 (ዋልታ) – በኢትዮጵያ በርካታ አለም አቀፍ እውቅና ያላቸው ሰዎች በኢትዮጵያ ውስጥ የእጣንና ሙጫ ደንን ከአደጋ ለመታደግ በሚደረገው ዘመቻ እየተሳተፉ እንደሚገኙ ተገለፀ፡፡
መቀመጫውን በሰሜን ምእራብ ኢትዮጵያ መተማ አድርጎ ደን ላይ የሚሰራ በጎ አድራጎት ድርጅት ነዋሪዎችን በማስተባበር 10 ሺህ ሄክታር መሬት የሚጠጋ የተጨፈጨፈ ደን መልሶ ለማልማት የመሳሪያ አቅርቦት ማድረጉ ተሰምቷል፡፡
በአካባቢው ያለው አብዛኛው መሬት በመራቆቱ ለምነቱን እያጣና ወደ በረሃነት እየተቀየረ በመምጣቱ የሙቀት መጠኑ ከፍ ማለቱን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል፡፡
ዝነኛ ሰዎችን ጨምሮ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሙያ ክሪስ ፓክሃምን፣ ተዋንያን ጆአና ሎምሌ እና ዞኤ ዋናማከርን ድጋፋቸውን ማሳየታቸውም ተጠቁሟል፡፡
የመተማ ደን በብዛት የያዘው የእጣንና ሙጫ ዛፍ የተለያዩ የዘይት ዓይነቶችን ለማምረት ያስችላልም ነው የተባለው።
የመተማ ደን ላይ መልሶ ደኑን ለማልማት የሚያስችል እርምጃዎች ካልተወሰደ በ20 ዓመታት ውስጥ ሊጠፋ እንደሚችል የተገለፀ ሲሆን፣ በነዋሪዎቹ ላይም አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል ተብሏል፡፡