በእንግሊዝ ለህዳሴ ግድብ ከ152 ሺሕ ፓውንድ ባላይ ገቢ ተሰበሰበ

ኅዳር 3/2014 (ዋልታ) በእንግሊዝ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከ152 ሺሕ ፓውንድ በላይ ገቢ መሰብሰቡ ተገለጸ፡፡
በእንግሊዝ የኢትዮጵያ ኤምባሲ “አንድ ሺሕ እራት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ” በሚል መሪ ቃል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር አካሂዷል፡፡
በመድረኩም በእንግሊዝ እና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ተሳትፈዋል፡፡
በዚህም ለህዳሴ ግድብ ከ152 ሺሕ ፓውንድ በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን በእንግሊዝ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡