በኦሮሚያ ክልል ሰንዳፋ ባሕላዊ የፈረስ ፌስቲቫል ተካሄደ

ጥር 29/2014 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል ሰንዳፋ ከተማ “ባሕላዊ የፈረስ ፌስቲቫል ለቱሪዝም ልማት” በሚል መሪ ቃል የፈረስ ስፖርት ፌስቲቫል ተካሄደ፡፡
በፌስቲቫሉ ላይ የተገኙት የቱሪዝም እና ስፖርት ሚኒስትሩ ቀጄላ መርዳሳ በኢትዮጵያ ታሪክ የኦሮሞ ፈረሰኞች በአገር ግንባታ ላይ ትልቅ ሚና እንደነበራቸው አውስተዋል።
በዝግጅቱ ከኦሮሚያ ክልል ልዩ ልዩ ዞኖች የተውጣጡ ፈረሰኞች የፈረስ ጉግስ፣ ሽምጥ ግልቢያ እና ባሕላዊ ጭፈራዎችን አቅርበዋል።
በፌስቲቫሉ ላይ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ሆነው ኢትዮጵያን ያጸኑ የኦሮሞ ጀግና ፈረሰኞች ተዘክረዋል።
እንየው ቢሆነኝ (ከሰንዳፋ)