በኦሮሚያ ክልል ቆላማ መሬት ላይ 130 ሺህ ሄክታር ስንዴ በመስኖ ማልማት መቻሉ የሚደነቅ ተግባር ነው-ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

በኦሮሚያ ክልል ቆላማ መሬት ላይ 130 ሺህ ሄክታር ስንዴ በመስኖ ማልማት መቻሉ የሚደነቅ ተግባር ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

በኦሮሚያ ክልል ቆላማ መሬት ላይ 130 ሺህ ሄክታር ስንዴ በመስኖ ማልማት መቻሉ የሚደነቅ ተግባር መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ክልል በመስኖ የሚለማ የስንዴ ማሳን ጎብኝተዋል፡፡

የተመዘገባው ስኬት በእቅድ ለማምረት የተያዘውን 300 ሺህ ሄክታር የስንዴ ምርት ለማሳካት እና ከውጭ የምናስገባውን ስንዴ በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የሚደረውን ጥረት ያፋጥናል ብለዋል።