በኮሮናቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ2 ሚሊየን አለፈ

በአለም በኮሮናበቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 2 ሚሊየን 18ሺ 417 መድረሱ ተገለጸ፡፡

እስካሁን በአለም ዙሪያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 94 ሚሊየን 336 ሺህ 471 ሲሆን ከዚህ ውስጥ 67 ሚሊዮን 367ሺህ 88 ሰዎች አገግመዋል፡፡

ከወርልድ ኦ ሜትር የተገኘው መረጃ እንዳለከተው በአለም አቀፍ ደረጃ በቫይረሱ ከሞቱት ውስጥ አሜሪካ 401ሺህ 856 ሞት በማስመዝገብ ቀዳሚ ስትሆን፣ ብራዚል 208 ሺህ 291 ሺህ ሞት በማስመዝገብ ሁለተኛ እንዲሁም ህንድ 152 ሺህ 130 ዜጎቿን በሞት በመነጠቅ በማጣት በሶስተኛ ደረጃ ትገኛለች።

በኢትዮጵያም በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2ሺህ 23 መድረሱ ታውቋል፡፡