በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ90 ሚሊየን አለፈ

በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 90 ሚሊየን 742 ሺህ 460 መድረሱን የዎርልድ ኦሜትር መረጃ አመልክቷል፡፡

በወረርሽኙ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር አንድ ሚሊየን 944ሺህ 460 ሲሆን፣ 64 ሚሊየን 881ሺህ 978 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው ማገገማቸው ተገልጿል።

ከዚህ ቁጥር ውስጥ አሜሪካ ከ22 ሚሊየን 917 ሺህ 334 የሚሆኑ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ዜጎች በማስመዝገብ በዓለም ቀዳሚ ደረጃ ይዛለች።

ከዚህ ቁጥር ውስጥ ከ383 ሺህ በላይ ዜጎቿ ሕይወት ሲያልፍ፣ 13 ሚሊየን በላይ ዜጎቿ ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል።

ሕንድ ከ10 ሚሊየን 467 ሺህ 431 በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች በማስመዝገብ በሁለተኛነት ስትቀመጥ፣ 151 ሺህ በላይ ዜጎቿ ሕይወታቸው አልፏል።

በሦስተኝነት የተቀመጠችው ብራዚል ከሰባት ሚሊየን በላይ ዜጎቿ በቫይረሱ ሲያዙ፣ የ200 ሺህ ያህል ዜጎቿ ሕይወት አልፏል።

ሩስያ እና ዩናይትድ ኪንግደም ከሦስት ሚሊየን በላይ እንዲሁም ፈረንሳይ፣ ቱርክ፣ ጣልያን እና ስፔን እያንዳንዳቸው ከሁለት ሚሊየን በላይ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች በማስመዝገብ ቀጣዮችን ደረጃዎች ይዘው ይገኛሉ፡፡