በደሴ ከተማ የጎዳና ላይ የኢፍጣር መርኃግብር ተካሄደ

 በደሴ ከተማ ሙስሊም ወጣቶች ማኅበር የተዘጋጀው ልዩ ”የአብረን እናፍጥር” የኢፍጣር መርኃግብር በደሴ ከተማ የተለያዩ ጎዳናዎች ላይ ተካሂዷል።
መርኃግብሩ ፍቅርንና አንድነትን ለማጠናከር ዓላማ ያደረገ መሆኑን የደሴ ከተማ ሙስሊም ወጣቶች ማኅበር ሊቀመንበር ይማም አህመድ ተናግሯል።
በኢፍጣር ዝግጅት ላይ የደሴ ከተማ ሙስሊም ማኅበረሰብ፣ የክርስትና እምነት ተከታዮች እና አቅመ ደካሞች ታድመዋል።
(ምንጭ፡- አሚኮ)