በጅማ ከተማ ከ300 ሚሊየን ብር በላይ የተገነቡ ፕሮጀክቶች እየተመረቁ ነው

ሰኔ 5/2013(ዋልታ) – በጅማ ከተማ ከ300 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተጠናቀቁ የመንገድ፤ የንፁህ መጠጥ ውሃ፤ የገበያ ማዕከላትና የህዝብ መናፈሻ ፓርክ ጨምሮ 15 የህዝብ ፕሮጀክቶች እየተመረቁ ይገኛል።

 

ከ 7.4 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ሁለት የገበያ ማዕከላት በዛሬው እለት የተመረቁ ሲሆን ለ 310 ሰዎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሏል።

 

የገበያ ማዕከላቱ ከ 100 ሺህ በላይ የከተማዋን ነዋሪዎች ማገበያየት የሚችል እንደሆነም ተግሯል።

 

እንደዚሁም በ55 ሚሊየን ብር የተገነባው 25 ሜትር የጎን ስፋት ያለው የ 3 ኪ.ሜ የከተማ የውስጥ ለውስጥ የጠጠር መንገድም ተመርቋል።

 

በተጨማሪም ከ 60 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የአዌቱ ወንዝ ዳርቻን ማልማት ፕሮጀክት የፊታችን ረቡዕ ይመረቃል ተብሏል።

በደረሰ አማረ