በጉራጌ ዞን ከ57 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶች ተመረቁ

ሰኔ 06/2013 (ዋልታ) – በጉራጌ ዞን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከ57 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደረገባቸው የልማት ፕሮጀክቶች ተመረቁ።
የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ እና የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል በጉራጌ ዞን ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከ24 ሚሊየን ብር በላይ የተገነባውን የመሀል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል መርቀው ከፍተዋል።
ሆስፒታሉ በ2003 ዓ.ም ግንባታውን ለማካሄድ የመሠረት ድንጋይ ቢጣልም በተለያዩ ምክንያቶች ተስተጓግሎ ቆይቶ በዛሬ ዕለት ለምረቃ በቅቷል።
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ከ33 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበትን የመሀል አምባ ኮንስትራክሽን እና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ መርቀው ይከፍታሉ፡፡
የመሀል አምባ ኮንስትራክሽን እና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በአቶ መሀመድ ገረሱ እና ቤተሰቦቹ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አማካኝነት ነው ተገንብቶ ለምረቃ በቅቷል።
(በዙፋን አምባቸው)