በጦላይ የምልምል ወታደሮች መመረቅ

በጦላይ የምልምል ወታደሮች መመረቅ

መስከረም 04/2014 (ዋልታ) የጦላይ ከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኛ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በመሰረታዊ ውትድርና ያሰለጠናቸውን ምልምል ወታደሮች አስመረቀ።

የማሰልጠኛ ማዕከሉ ዋና አዛዥ ብረጋዴል ጀነራል ጡምሲዳ ፊተሎ ምልምል ወታደሮቹ በቆይታቸው ልዩ ልዩ ሥልጠናዎች ስለመውሰዳቸው ተናግረዋል።

በሥልጠናው የስነልቦና እንዲሁም በወታደራዊ ቴክኒክ ክህሎት በቂ ስልጠና ማግኘታቸውንም ገልጸዋል። በዚህም መሰረታዊ የውትድርና አቅም ተፈጥሯል ብለዋል።

ከሰልጣኞቹ መካከል ወደ አየር ኃይል ኢንጅነሪንግ ዘርፍ የተቀላቀሉ መኖራቸውም ተጠቁሟል።

የመከላከያ ህብረት የሰው ሀብት መምርያ ኃላፊ ሜጀር ጀነራል ሀጫሉ ሸለመ በበኩላቸው፣ አሸባሪው ትህነግ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ያስችለኛል ያለውን እኩይ ተግባራት በሙሉ እየፈጸመ መሆኑን አንስተው፣ ተመራቂ ወታደሮች የሀገራቸውን ህልውና ለማስቀጠልና በአሸባሪው ቡድን እየተገደሉ፣ እየተፈናቀሉ ያሉ ዜጎችን ለመታደግ በተባበረ ክንድ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማስወገድ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በመስከረም ቸርነት