በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጅማ አባጅፋርን 3 ለ 2 አሸነፈ

በሰባተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጅማ አባጅፋርን 3 ለ 2 አሸነፈ ።

የሰባተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚሪሊግ የወንዶች እግር ኳስ ጨዋታ ጅማ አባጅፋር ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታቸውን አካሂደዋል።

በጨዋታውም ቅዱስ ጊዮርጊስ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

በጨዋታው ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሶስቱንም ጎሎች ጌታሀን ከበደ በማስቆጠር ሃትሪክ ሰርቷል።

ጅማ አባጅፋርን ከሽንፈት ያልታደጉትን ሁለቱን ጎሎች ደግሞ ሮባ ወርቁና ቤካም አብደላ አስቆጥረዋል።

ፕሪሚሪሊጉ ዛሬ ከሰዓትም የሚቀጥል ሲሆን ወላይታ ድቻ ከሰበታ ከተማ የሚጫወት መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።