ፕሬዝዳንት ባይደን እና ፕሬዝዳንት ፑቲን በስልክ ተወያዩ

 ባይደን እና ፑቲን

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያዩ፡፡

ባይደን ከፑቲን ጋር በነበራቸው የመጀመሪያ የስልክ ውይይት በምርጫ ላይ ተጽእኖ መፍጠር ዙሪያ ላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል ነው የተባለው።

በሁለቱ መሪዎች በውይይት በአሁኑ ወቅት በሩሲያ እየተካሄደ ስላለው መንግሥታዊ ተቃውሞ እና ስለ አሜሪካ-ሩሲያ ኒውክለር ስምምነት የተነሱ አጀንዳዎች እንደነበሩ የሩሲያ መንግሥት መግለጫ አመልክቷል።

በመግለጫው እንደተገለጸው ሁለቱ መሪዎች ወደፊት ግንኙነታቸውን ለማስቀጠል ስለመስማማታቸውም ተገልጿል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡