ብሔራዊ ቡድኑ ለ 2023 አፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ

ግንቦት 25/2014 (ዋልታ) ኮትዲቯር ለምታዘጋጀው የ 2023 አፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ለማድረግ ወደ ማላዊ የሚጓዙት ዋልያዎቹ ዝጅት አሰመልክቶ መግለጫ ተሰጥቷል።
የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ውበት አባተ በመግለጫው ቡድኑ ሁለት የወዳጅነት ጨዋታ ማድረጋቸውን እና ክፍተቶችን ለመለየት ዝግጅት ማድረጋቸው ገልጸዋል።
ብሔራዊ ቡድኑ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከማላዊ እና ከግብፅ ጋር ያደርጋል።
ቡድኑ ጨዋታውን በሜዳው ባለማድረጉ ከ 50 ሺሕ ዶላር በላይ ለማውጣት መገደዱም ተገልጿል።
በሚኪያስ ምትኩ