ቦርዱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ የምርጫ ምልክትን ይፋ አደረገ

ሚያዚያ 01/ 2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ የምርጫ ምልክትን ይፋ አድርጓል።

ከስድስተኛው አጠቃላይ ምርጫ ጋር በጋራ የሚከናወነው ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ የምርጫ ምልክትም አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት የተያያዙ እጆች የኮንታ ልዩ ወረዳ፣ የምዕራብ ኦሞ ዞን፣ የቤንች ሸኮ ዞን፣ የካፋ ዞን፣ ዳውሮ ዞን እና የሸካ ዞን ከደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ወጥተው የጋራ አንድ ክልል መመስረታቸውን እደግፋለሁ የሚለውን እንደሚወክሉ ገልጿል፡፡

በተጨማም የጎጆ ቤት የኮንታ ልዩ ወረዳ፣ የምዕራብ ኦሞ ዞን፣ ቤንች ሸኮ ዞን፣ የካፋ ዞን፣ ዳውሮ ዞን እና የሸካ ዞን ከደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል አካል ሆነው መቀጠላቸውን እደግፋለሁ የሚለውን እንደሚወክልም አስታውቋል፡፡