ተቋርጠው የነበሩ ሜታ አገልግሎቶች ተመለሱ

ለሰዓታት ተቋርጠው የነበሩት የሜታ አገልግሎቶች ዳግም መስራት ጀመሩ።

የሜታ አገልግሎቶች በምን ምክንያት እንደተቋረጡ እስካሁን የተገለጸ ነገር የለም።

ዛሬ ከአመሻሽ ጀምሮ አገልግሎቶቹ ተቋርጠው መቆየታቸውን ከተለያዩ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ለማረጋገጥ ተችሏል።

አካውንቶቹ ሎግ አውት (log out) ተደርገው በራሱ ሰዓት የወጡ ሲሆን በሰዓቱ ዳግም መግባት እንዳልተቻለም ከተጠቃሚዎች የደረሰን መረጃ ያሳያል።