ትምህርት ቤቶች ደረጃውን የጠበቀ የመጠጥ ውሃና የመፀዳጃ ቤት እንዲኖራቸው የሚያስችል መመሪያ ተዘጋጀ

 

የካቲት 25/2013 (ዋልታ) – ትምህርት ቤቶች ደረጃውን የጠበቀ የመጠጥ ውሃና የመፀዳጃ ቤት እንዲኖራቸው የሚያስችል መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ትግበራ መግባቱ ተገለፀ።

መመሪያውን የትምህርት ሚኒስቴር ከዩኒሴፍና ፒ ኤስ አይ በጋራ በዩኒሴፍ በገንዘብና በቴክኒክ ድጋፍ የተዘጋጀ መሆኑን አንስተው በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ውስጥም እየተተገበረ መሆኑንም ተጠቁሟል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዬን ማቲዮስ መመሪያው የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል ያግዛል ሲሉ ገልፀው መመሪያው እንዲዘጋጅ ላደርጉት አካላትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

እንዲሁም የትምህርት ሚኒስቴር፣ የዩኒሴፍና የፒ ኤስ አይ ሃላፊዎች በተገኙበት የተዘጋጀውን መመሪያ ርክክብ መደረጉን ትምህርት ሚኒሰቴር አስታውቋል።