ቻይና ሶስት ልጆች የመውለድ ፖሊሲን አጸደቀች

ግንቦት 23/2013 (ዋልታ) – ቻይና ተጋቢዎች ከሁለት በላይ ልጆች እዳይወልዱ የሚያግደው የቤተሰብ ህግ በማሻሻል ሶስት ልጆች እንዲወልዱ ፈቅዳለች፡፡
ማሻሻያውን በፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ መጽደቁን ሺንዋ ዘግቧል፡፡
ቻይና ይህን ውሳኔ ያስተላለፈችው የህዝብ ብዛቷ በአስር ዓመት ውስጥ በዝቅተኛ ፍጥነት ማደጉን በተያዘው ወር መጀመሪያ ከወጣው የሕዝብ ቆጠራ በኋላ ነው ተብሏል፡፡
ባለፈው ዓመት 12 ሚሊየን የሚጠጉ ሕፃናት ተወልደዋል፤ ይህም በ2016 ከነበረው 18 ሚሊየን ጋር ሲነፃፀር እጅግ የቀነሰ ሲሆን ከ1960 ወዲህ የተመዘገበው የልደት ቁጥርም ዝቅተኛ መሆኑን የህዝብ ቆጠራው ውጤት አመላክቷል፡፡
የህዝብ ቆጠራው ውጤት ከወጣ በኋላ ቻይና የቤተሰብ ፖሊሲ ህጓን በሰፊው ታሻሽላለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡