ናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ 2ኛውን የውሃ ሙሌት በተመለከተ ያወጣው መግለጫ ተቀባይነት የሌለው መሆኑ ተገለጸ

ሰኔ 07/2013 (ዋልታ) – ናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ በካምፓላ ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የህዳሴ ግድብ እንዳትሞላ ያወጣው መግለጫ የሲቪክ ማህበራትን ሚና የማያሳይና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቪክ ማህበራት አስታወቀ፡፡

በዛሬው እለት የኢትዮጵያ ሲቪክ ማህበር በጉዳዩ ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ኢትዮጵያ በዓባይ ውሃ ያላትን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሀገሪቱ የሚገኙ ሲቪክ ማህበራት የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ በመግለጫው ተነስቷል።

ማንኛውም ቡድን በናይል ተፋሰስ ውስጥ ባሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መካከል አብሮነትንና ትብብርን ለማራመድ የሚመርጥ ከሆነ የናይል ተፋሰስ ዲስኩር የመጀመሪያ የምክክር መድረክ  መደረግ እንዳለበት ማህበሩ በመግለጫው አውስቷል።

ኢትዮጵያውያን ውሃውን በብቸኝነት የመጠቀም ፍላጎት እንደሌላትም ተመላክቷል፡፡

(በዙፋን አምባቸው)