አሜሪካ በሌሎች አገራት ጉዳይ ጣልቃ እንዳትገባ ሩሲያ ጥሪ አቀረበች

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ

የካቲት 26/2013 (ዋልታ) – የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሌሎች አገራት ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ጣልቃ አለመግባት በቃላት ሳይሆን በተግባር መሆን እንዳለበት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

አሜሪካ የአጋሮቿን ፍላጎት ከግምት የማታስገባ ከሆነ በሌሎች አገራት ጉዳይ ጣልቃ ያለመግባት ጉዳይ አዋጅ ብቻ ሆኖ የሚቀር እንደሚሆን ሩሲያ ገልጻለች፡፡