አሜሪካ ወደ ፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት መመለሷን አስታወቀች

የካቲት 12/2013 (ዋልታ)– አሜሪካ ወደ ፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት መመለሷን አስታውቃለች።

አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት ቃል በገቡት መሰረት አሜሪካ ወደ ስምምነቱ ዳግም ተመልሳለች።

የፕሬዝዳንቱን ውሳኔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቶኒ ብሊንከን ዛሬ ይፋ አድርገዋል።

ባለፈው ዓመት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቸው ከፓሪሱ ስምምነት መውጣቷን እና ከስምምነቱን በይፋ በመውጣት የመጀመሪያዋ እና ብቸኛዋ ሀገር መሆኗ የሚታወስ ነው፡፡

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌንኬን በትዊተር ገጻቸው ላይ “የአየር ንብረት ቀውስን ለመዋጋት ጥሩ ቀን” ያሉ ሲሆን አሜሪካ የአየር ንብረት ቀውሱን የመቋቋም  አቅሟን ለመገንባት በዓለም ዙሪያ ካሉ አጋሮቻቸው ጋር በትብብር ለመስራት ጊዜ እንደማታጠፋ ቃል መግባታቸውን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡