አሸባሪው ህወሀት በአፋር ህዝብ ላይ ጦርነት ከፍቷል

ሐምሌ 10/2013 (ዋልታ) – አሸባሪው የህወሀት ጁንታ የሽብር አድማሱን ወደ አፋር በማስፋት የአፋር አርብቶ አደር ህዝብ ላይ ጦርነት ከፍቷል።

ይህ እኩይ ቡድን በዳር ድንበር አስከባሪው በአፋር አርብቶ አደር ህዝብ ላይ በፈንቲ ረሱ ዞን ያሎ ወረዳ በኩል የከፈተውን ጦርነት መክፈቱን ከአፋር ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

የአፋር ክልል ህዝብ ከፀጥታ ሀይሉ ጎን በመቆም በፈንቲ ረሱ ያሎ ወረዳ በኩል የተከፈተውን ጦርነት እንዲመክት በንቃት አካባቢውን በመቃኘት ከአካባቢው የፀጥታ ሀይል ጋር በትብብር እንዲሰራ ጥሪ ቀርቧል፡፡