አሸባሪው የሕወሓት ቡድን የዘረፈውን ነዳጅ በአፋጣኝ እንዲመልስ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ድርጅት ጠየቀ

ዴቪድ ቢስሌይ

ነሐሴ 19/2014 (ዋልታ) አሸባሪው የሕወሓት ቡድን የዘረፈውን 570 ሺሕ ሊትር ነዳጅ በአፋጣኝ እንዲመልስ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ድርጅት ጠየቀ።

የድርጅቱ ዋና ኃላፊ ዴቪድ ቢስሌይ በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ተቋማቸው ነዳጁን ካላገኘ ሚሊዮኖች ለረሃብ ሊጋለጡ እንደሚችል ገልጸው ቡድኑ የዘረፈውን ነዳጅ በአፋጣኝ እንዲመለስ ጠይቀዋል።

የሽብር ቡድኑ ድርጊትም ነውረኛና የሚያስቆጣ መሆኑን ገልጸዋል።

ሕወሓት መቐለ ከሚገኘው ከዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን 12 ታንከር (570 ሺሕ ሊትር) ነዳጅ መዝረፉን የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ የአንቶኒዮ ጉተሬስ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪክ ትላንት ማምሻውን መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW