አንዲት እናት ዘጠኝ ልጆችን ወለደች

ሚያዚያ 27/2013 (ዋልታ) – በማሊ አንድ እናት በአንድ ጊዜ ዘጠኝ ልጆች በሰላም መገላገልዋ ተገለጸ።

የማሊ ጤና ሚኒስትር ፋንታ ሲብያ እንደገለፁት የ25 አመቷ ሃሊማ ሲያስ በሞሮኮ ሆስፒታል 5 ሴት እና 4 ወንዶችን በሰላም ተገላግላለች፡፡

የህፃናቱ እናት በማሊም ሆነ በሞሮኮ በተደረገላት የአልትራሳውንድ ምርመራ መሰረት 7 ልጆች እንደምትወልድ ቢጠበቅም ሁለቱ ልጆች ግን አለመታየታቸውን ጤና ሚኒስትሯ ገልፀዋል፡፡

የሆስፒታሉ ጤና ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ሲብያ እንደገለፁት እናትየዋና ህፃናቱም በሙሉ ጤንነት ላይ የሚገኙ ሲሆን ከተወሰኑ ሳምንታት በኋላ ወደ ቤታቸው እንደሚመለሱ ከቢቢሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡