ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ፖላንድ በተካሄደው የአለም የቤት ውስጥ የዙር ውድድር ድል አደረጉ

አትሌት ሀምታም አለሙ

የካቲት 11/2013 (ዋልታ) – ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ፖላንድ ቶሩን በተካሄደው የአለም የቤት ውስጥ የዙር  ውድድርን  በድል አጠናቀዋል።

በ800 ሜትር ውድድር የተካፈለችው  አትሌት ሀምታም  አለሙ የአለም ሁለተኛውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፋለች።

አትሌት  ሀብታም አለሙ 1 ደቂቃ ከ58 ሴኮንድ 19 የገባችበት ሰዓት ነው።

ጠንካራ ፉክክር በታየበት የ3000 ሜትር ውድድር አትሌት ለምለም ሀይሉ ኬንያዊቷን ቤትሪስ ቼብኮይችን አስከትላ አሸንፋለች።

አትሌት ለምለም ውድድሩን ለማጠናቀቅ 8 ደቂቃ 31 ሴኮንድ 24 ፈጅቶባታል።

ኬንያዊቷ አትሌት ቤትሪስ ቼብኮይች ከሶስት ቀናት በፊት ሞናኮ በተካሄደው የ5 ኪሜ የጎዳና ላይ ሩጫ የአለም ክብረወሰን ማሻሻሏ ይታወሳል።

እንዲሁም አትሌት ፋንቱ  ወርቁ ውድድሯን በሶስተኝነት ማጠናቀቅ ችላለች።

በዚህ ውድድር  የማሸነፍ ቅድመ  ግምት አግኝታ የነበረው አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ሩጫውን ማጠናቀቅ ሳትችል ቀርታለች።

እንዲሁም የ5000 ሜትር ውድድር ኮከቡ አትሌት ሰለሞን ባረጋ በ1500 ሜትር ባደረገው የምሽቱ  ውድድር የቦታውን ክበረወሰን ጭምር በማሻሻል ነው ያሸነፈው።

አትሌት ሰለሞን ባረጋ የገባበት ሰዓት 3 ደቂቃ ከ32 ሴኮንድ 97 ነው።

(ምንጭ:-አፍሪካን አትሌቲክስ ዩናይትድ)