ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፉ ሀገራዊ ዐቅም በመፍጠር የውጪ ምንዛሬ የማግኘት አቅሟን ታጠናክራለች – ጠ/ሚ ዐቢይ

ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ማምረት የሚያስችል ሀገራዊ ዐቅም በመፍጠር የውጪ ገበያ እና የውጪ ምንዛሬ የማግኘት አቅሟን እንደምታጠናክር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ኢትዮጵያ እሴቶችን በመጨመር በየአካባቢው የሚገኙ ባህላዊ ማዕድን አውጪዎችን እና ማኅበረሰቦችን ሕይወት ማሻሻል የሚያስችሉ በርካታ የተፈጥሮ ማዕድን የታደለች ሃገር መሆኗን ጠቅሰዋል፡፡

ወርቅ፣ ቤዝ ብረቶች፣ ፖታሽ፣ ታንታለም፣ ሰንፔር፣ ኤመራልድ እና ኦፓልም በዚህ ረገድ ተጠቃሽ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

አያይዘውም በማዕድን ዘርፍ ማምረት የሚያስችል ሀገራዊ ዐቅምን በመፍጠር የውጪ ገበያ እና የውጪ ምንዛሬ የማግኘት አቅም ይጠናከራልም ነው ያሉት፡፡