ኢትዮጵያ የሴካፋ ውድድር ሻምፒዮን ሆነች

የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን

ኅዳር 1/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዙሩ ካደረጋቸው 4 ጨዋታዎች ሁሉንም በአሸናፊነት በማጠናቀቅና 12 ነጥብ በመያዝ ሻምፒዮን ሆነ።

ቡድኑ 12 ነጥብ ካለው ዩጋንዳ አቻው ጋር ባደረገው የመጨረሻውን የዋንጫ ጨዋታ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ነው ሻምፒዮን መሆን የቻለው።

በዩጋንዳ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የምስራቅና መካከለኛ አፍሪካ ሀገራት ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድኖች ውድድር በስድስት ሀገራት መካከል በዙር ሲካሄድ ቆይቶ ትላንት በተደረጉ ሦስት የመጨረሻ ጨዋታዎች ፍፃሜውን አግንቷል።

በውድድሩ ኢትዮጵያ ሻምፒዮን በመሆን የዋንጫ እና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ስትሆን ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን በመያዝ የብርና የነሃስ ሜዳሊያ ተሸላሚ መሆናቸውን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡