ኢትዮ ቴሌኮም በደቡብ ምዕራብ ሪጅን ከተሞች የ4ጂ ኤል.ቲ .ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ጀመረ

      የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፍጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ
 
ሰኔ 08/2013 (ዋልታ) – ኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ የዳታ አጠቃቀም በሚታወቅባቸው 103 ከተሞች የ4ጂ ኤል. ቲ. ኢ አገልግሎትን ለማስፋፋት በያዘው ዕቅድ በደቡብ ምዕራብ ሪጅን በሚገኙ 8 ከተሞች በጅማ፣ አጋሮ፣ በደሌ፣ ቦንጋ፣ ኮይሻ፣ መቱ ፣ሚዛን፣ ማሻ እና ቴፒ ነው ማስፋፍያ ፕሮጀክቱን ያስጀመረው::
በኩባንያው ጥናት መሠረት በደቡብ ምዕራብ ሪጅን የሚኖሩ ዜጐች 24 በመቶ የሚሆኑት የስማርት ፎን ተጠቃሚ በመሆናቸው ዛሬ የተጀመረው የ4ጂ አገልግሎት ለተጠቃሚዎቹ ወሳኝ ነው ተብሏል።
በተለይም የንግድ ስራዎችን ጨምሮ ለተለያዩ ስራዎች ቅልጥፍና የ4ጂ ኤል.ቲ .ኢ አገልግሎት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ነው የተባለው::
ኢትዮ ቴሌኮም እስካሁን ባደረጋቸው የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት ማስፋፊያ ስራዎች የዛሬውን የደቡብ ምዕራብ ሪጅንን ጨምሮ 52 ከተሞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል።
ኩባንያው ከአገልግሎት ተደራሽነት በተጨማሪ የኔትዎርክ ጥራትን ለማረጋገጥ እየተጠጋ ነው ሲሉ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፍጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገልጸዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አክለውም ኢትዮ ቴሌኮም የ3 አመት ስትራቴጁ ቀርፆ እየሠራ መሆኑን ገልጸው በቅርቡ የ 5ጂ አገልግሎትን ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ያደረጋል ብለዋል።
(በሜሮን መስፍን)