ኢትዮ ቴሌኮም የ4G ኤልቲኢ አገልግሎትን በሰሜን ምስራቅ ምስራቅ ሪጅን በአራት ከተሞች አስጀመረ

ግንቦት 26 / 2013 (ዋልታ) – የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎትን በላቀ ፍጥነት መጠቀም የሚያስችለውን የ4G ኤልቲኢ አገልግሎትን በሰሜን ምስራቅ ምስራቅ ሪጅን ከተሞች ሰመራ፣ ሎጊያ፣ አዋሽ 7ኪሎ እና አሳይታ ከተሞች አስጀምሯል።
ይህም ኩባንያው በበጀተ ዓመቱ ከፍተኛ የዳታ አጠቃቀም በሚታይባቸው 103 ከተሞች ላይ የ4G ኤል ቲ ኢ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የያዘው ዕቅድ አካል መሆኑን የኢትዮ ቴሌኮም ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።
እስካሁንም 44 ከተሞች የ4G ኤል ቲ ኢ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸው እና ከዚህ ቀደም ከነበረው የ3G አገልግሎት በ3እጥፍ ፈጣን መሆኑንም ተናግሯል።
አገልግሎቱ የላቀ ፍጥነትን ጨምሮ የደንበኞችን አገልግሎት ዲጂታላይዝድ ለማድረግ፣ምርታማነትን ለማሳደግ እና አጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎት ላይ ያላቸውን ተሞክሮ በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደጉም ተገልፃል።
የኢንተርኔት ማስፋፊያ በማህበራዊ ትስስር ገፅ አማካኝነት ለዜጎች ፈጣን መረጃን ከማግኘት አንፃር አስተዋፅኦው ከፍተኛ መሆኑን ያነሱት ስራ አስፈፃሚዋ ሁሉም አካል በሃላፊነት እንዲጠቀም አሳስበዋል።
አሁን ላይ 25 ሚሊዮን የሞባይል ዳታ ተጠቃሚ መኖሩን ተጠቁሟል፡፡ በመጨረሻም ለቁጥሩ ማደግ ደግሞ የኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የተሰራው የማስፋፉያ ስራ ትልቁን ድርሻ ይወስዳል ተብሏል።
(በትዕግስት ዘላለም)