ኢዜማ ብርሃኑ ነጋን (ፕ/ር) በድጋሚ የፓርቲው መሪ አደርጎ መረጠ

ብርሃኑ ነጋን (ፕ/ር)

ሰኔ 27/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ሰኔ 26 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ አመሻሽ ባካሄደው አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው በየዘርፉ ተፎካካሪ እጩዎች ቀርበው የምረጡኝ ቅስቀሳ ካደረጉ በኋላ አሸናፊዎቹን እኩለ ሌሊት ገደማ አሳውቋል፡፡

በዚሁ መሰረት ፓርቲው ብርሀኑ ነጋን (ፕ/ር) መሪ እና ዮሐንስ መኮንንን ምክትል መሪ አድርጎ መርጧል፡፡

ጫኔ ከበደ (ዶ/ር) እና አማኑኤል ኤርሞ (ዶ/ር) ደግሞ የፓርቲው ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ኢዜማ አበበ አካሉን ዋና ፀሀፊ አድርጎ የመረጠ ሲሆን በሚስጥር በተካሄደው የድምጽ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት በሌሎችም ዘርፎች ፓርቲውን የሚመሩ አባላትን ጭምር መርጦ መሰየሙን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW