ኤጀንሲው የመሬት ይዞታን አረጋግጦ በህጋዊ ካዳስተር ሲስተም ለመመዝገብ እወጃ ማካሄዱን አስታወቀ

ጀማል ሀጅ

ሚያዝያ 11/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኙ 25 ቀጣናዎች እና 112 ሰፈሮች ላይ በመደዳ የመሬት ይዞታን አረጋግጦ በህጋዊ ካዳስተር ሲስተም ለመመዝገብ እወጃ ማካሄዱን አስታወቀ።

በኤጀንሲው የይዞታ ማረጋገጥ አድራሻ ዝርጋታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ጀማል ሀጅ በሰጡት መግለጫ ዘንድሮ ለ5ኛ ጊዜ በሚያካሂደው የይዞታ ማረጋገጥ ሥራ በአስራ አንዱ ክፍለ ከተሞች በተመረጡ 25 ቀጣናዎች ውስጥ የሚገኙ 21 ሺሕ 436 ይዞታዎችን እና 40 ሺሕ 625 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ከሚያዝያ 5 እስከ ጳጉሜ 5 ድረስ ባሉት አምስት ወራት ውስጥ በመስክ እና በሰነድ አረጋግጦ በህጋዊ ካዳስተር ሲስተም ለመመዝገብ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።

ባለይዞታዎች ኤጀንሲው አረጋግጦ ላልመዘገበው ይዞታ ምንም አይነት ህጋዊ ዋስትና እና ከለላ የማይሰጥ መሆኑን በመገንዘብ ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ከሚያዝያ 20 ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች በሚያወጡት ፕሮግራም መሰረት የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ እንዲያቀርቡ ጥሪ ተላልፏል።

በሜሮን መስፍን

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW