ከሕወሓት ጋር ያበሩ የአፋር ክልል የቀድሞ አመራሮች በአሸባሪነት መፈረጅ

ነሐሴ 26/2013 (ዋልታ) – የአፋር ክልል ምክር ቤት ከሕወሓት የሽብር ቡድን ጋር ያበሩ የክልሉን አመራሮች በአሸባሪነት ፈረጀ፡፡

ኢቢሲ እንደዘገበው አገራዊ ለውጡን ተከትሎ ግላዊ ጥቅምን ከሕዝብ አስበልጠው ከሕወሓት ጋር ያበሩት እነዚህ ጥቂት ባንዳዎች የአፋር ሕዝብ ጠላት መሆናቸውን በይፋ አሳይተዋል ብሏል፤ ምክር ቤቱ።

በዚህም እነዚህ ሕዝብ እና አገርን የካዱ ባንዳዎች በአፋር እና በተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በፈፀሙት ክህደት የደረሰውን ጉዳት ታሳቢ በማድረግ በአፋር ክልል ያለ ሃብት እና ንብረታቸውን እንዳያንቀሳቅሱ ሲል ምክር ቤቱ ወስኗል።

ሆኖም በአሸባሪነት መዝገብ የሰፈሩት የቀድሞ አመራሮች ስም ዝርዝር በዘገባው አልተጠቀሰም፡፡