ከምርጫ ጋር ተያይዞ የሚከሰትን ወንጀል ለመከላከል የሚረዳ የሁለት ቀናት ስልጠና ተዘጋጀ

የኢፌዲሪ ጠቅላይ አቃቢ ህግ  ከምርጫ ጋር ተያይዞ የሚከሰትን ወንጀል ለመከላከል ይረዳ ዘንድ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ስልጠና አዘጋጅቷል።

ም/ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ፈቃዱ ሰጠኝ ቀጣዩን አገራዊ ምርጫ ተከትሎ ሊከሰት የሚችልን  ወንጀል ለመከላከል አቃቢ ህግ ፣ፓሊስ እና የምርጫ ቦርድ በጋራ መስራት እንዳለባቸው ገልጸው ከቀበሌ ጀምሮ ያሉ አመራሮች  እና ባለሙያዎች አዋጆችን ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡

በህገመንግስቱ ውስጥ የተካተቱትን አንቀፆች ጨምሮ አዋጆችን ተግባራዊ ማድረግ ፍትሀዊ የምርጫ ሂደት እንዲኖረን ሰፊ መንገድ ይፈጥራል ያሉት ም/ጠቅላይ አቃቢ ህጉ ይህ ለሁለት ቀናት የሚቆየው ስልጠናም ባለሙያወቹ ብቁ እንዲሆኑ ያደርጋል ብለዋል።

በስልጠናው ላይ የሚመለከታቸው አካላት ተሳታፊ ሲሆኑ በአንቀፆች እና  ከምርጫ ጋር ተያይዞ የሚከሰትን ወንጀል ለመከላከል በሚያስችሉ የወንጀል ምርመራ ስርዓቶች ዙሪያ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚካሄድባቸው ተገልጿል።

(በቁምነገር አህመድ)