ከሳኡዲ አረቢያ ከ1 ሺሕ 270 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

መጋቢት 26/2014 (ዋልታ) በሳኡዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ1 ሺሕ 270 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡
በሳውዲ አረቢያ ሪያድ እና ጅዳ የሚገኙ ዜጎች ወደ ሀገራቸው የመመለሱ ተግባር አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡
በዛሬው ዕለትም ከሳኡዲ አረቢያ ጂዳ በተደረጉ ሦስት በረራዎች 269 ህጻናትን ጨምሮ 1 ሺሕ 270 ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።
ተመላሾች ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።