ከተማ አስተዳደሩ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔዎችን አሳለፈ

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመወያየት ውሳኔዎችን አሳልፏል።

በዚሁ መሰረት፦

1- የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል ለታካሚ ህፃናት እና ቤተሰቦች ስቃይን ለመቀነስ በነፃ አገልግሎት እየሰጠ ያለውን የበጎ አድራጎት ስራ በዘላቂነት ለመደገፍ ያስችል ዘንድ የታክስ የዕዳ ምህረትና ከኪራይ ገቢ ግብር ነፃ እንዲደረግ ካቢኔው ወስኗል።

2- በከተማዋ ለሚገኙ ዝቅተኛ የተማሪዎች የምገባ ስራ ላይ ለተሰማሩ እናቶች የአንድ አመት የገቢ ግብር ወጪን የዕዳ ምህረት እንዲደረግም ውሳኔ ተላልፏል።

3-በመጨረሻም ከተማ አስተዳደሩ ለቢሮ አገልግሎት በአመት 746 ሚሊዮን ብር በላይ የኪራይ ወጪ የሚያወጣባቸውና እነዚህ ቢሮዎች በተበታተኑ ቦታዎች በመሆናቸው ለተገልጋይ ከፍተኛ እንግልትን እና የህዝብ ገንዘብ ብክነት እያስከተለ ስለሆነ እነዚህ ቢሮዎች ሁሉንም ሰብሰብ አድርጎ በሁለት ክላስተር ለተገልጋዮች ለአገልግሎት ምቹ እና ወጪ ቆጣቢ የሚሆኑ ቢሮዎች ግንባታ ፕሮጀክት እንዲጀመር መወሰኑን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።