ከንቲባ አዳነች ለርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል

ጥቅምት 12/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አበቤ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ለተሾሙት ኦርዲን በድሪ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

“የሀረሪ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ታላቅ የህዝብ አደራን ለተቀበሉት አቶ ኦርዲን በድሪ በራሴና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስም እንኳን ደስ አለዎት” ሲሉ ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ስኬታማ የአገልጋይነት ዘመን ይሁንልዎት ሲሉም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡