ከወጪ ንግድ በ8 ወራት 2.1 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ

መጋቢት 20/2013 (ዋልታ) – በ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስምንት ወራት የወጪ ንግድ አፈጻጸም ይገኛል ተብሎ ከታሰበው 2.55 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር 2.1 ቢሊየን ዶላር መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የወጪ ንግድ አፈጻጸሙ የዕቅዱን 82 በመቶ ያሳካ ሲሆን ይህም በ2012 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው 1.81 ቢሊየን ዶላር ጋር ሲነጻጸር የ16 በመቶ ወይም የ290 ሚሊየን ዶላር ብልጫ እንዳለው ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡