ከ37 ሚሊየን በላይ ዜጎች የማህበረሰከ37 ሚሊየን በላይ ዜጎች የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ተጠቃሚ ሆነዋልብ አቀፍ ጤና መድህን ተጠቃሚ ሆነዋል

መጋቢት 20/2013 (ዋልታ) – ከ37 ሚሊየን በላይ ዜጎች የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ተጠቃሚ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ጤና መድህን ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

የኤጀንሲው የአባላት ምዝገባና መዋጮ ዳይሬክተር አቶ ጉደታ አበበ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ37 ሚሊየን ማለፉን እና ይህም ከአምናው ጋር ሲነጻጸር የ5 ሚሊየን ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል።

ከእነዚህ ውስጥ 7 ሚሊየን 32 ሺህ የሚሆኑት መክፈል የማይችሉ ሲሆኑ ወጪያችው በመንግሰት የሚሸፈን ነው ማለታቸውን ከኢትዮጵያ ጤና መድህን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡