ኪነ ጥበብ ምንጊዜም ከኢትዮጵያ ጀግንነት ጋር ናት – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

ነሐሴ 11/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኪነ ጥበብ ምንጊዜም ከኢትዮጵያ ጀግንነት ጋር ናት አሉ፡፡

“ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ መቼም፣ የትም፣ በምንም” በሚል መሪ ቃል የብሔራዊ ቴአትር፣ የኦሮሞ የባህል ማዕከልና የአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች በወታደራዊ ማሠልጠኛዎች ተገኝተው ዝግጅቶችን አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዝግጅቶቹን ላቀረቡ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች ምስጋናቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አቅርበዋል፡፡

ሌሎችም ከያንያን አርአያነታችሁን እንደሚከተሉ ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉ ነው የገለጹት።