ዓለም አቀፍ የነርሶች ቀን እየተከበረ ነው

ግንቦት 04/2013 (ዋልታ) – ዓለም አቀፍ የነርሶች ቀን “ነርስ የመሪነት ድምጽ እና የነገው የጤና አገልግሎት ትኩረት” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡
ቀኑን በማስመልከት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመዋጋት ነርሶች በግንባር ቀደምትነት በመሰለፍ እና በተለያዩ ጤና ተቋማት በሚሰጡት እንክብካቤ ለታካሚዎች መዳንና ማገገም የሚጫወቱት ሚና ወሳኝ በመሆኑ ሁሉንም ነርሶች አመስግነዋል፡፡
“ሳትታክቱ ለማህበረሰባችሁ ለምትሰጡት አገልግሎት ሁሌም እናከብራችኃለን” በማለት ዶ/ር ሊያ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።