የህዳሴ ግድቡ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በታችኞቹ የተፋሰስ ሃገራት ላይ ምንም ተጽዕኖ አይኖረውም – የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ

ግንቦት 11/2013 (ዋልታ) – ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በታችኞቹ የተፋሰስ ሃገራት ላይ ምንም አይነት ተጽዕኖ እንደማያሳድር የግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሹክሪ ገለጹ፡፡

የሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በታችኛው የተፋሰሱ ሃገራት ላይም ይሁን በአስዋን ግድብ ላይ የሚያደርሰው አሉታዊ ተጽዕኖ እንደማይኖር ሳሚ ሹክሪ ለግብጻዊያን አረጋግጠዋል፡፡

ሚኒስትሩ ናሻት አል ደሂ ከተሰኘ የተሌቪዥን ጣቢያ ጋር በነበራቸው ቆይታ የህዳሴ ግድቡ የሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በግብጽ ጥቅም ላይ ምንም ተጽእኖ እንደማያሳድር እርግጠኞች ነን ብለዋል፡፡

(ምንጭ፡- ኢጂፕት ኢንዲፔንደንት)