ሐምሌ 14 /2012 (ዋልታ) – ኢትዮጵያ ታላቁን የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ብታካሂድም ወደ ሱዳን የሚፈሰው የውሃ መጠን እንዳልቀነሰባት ሱዳን አስታወቀች።
የሱዳን የአል-ሩሳይረስ ግድብ ዳይሬክተር ሀሚድ ሞሃመድ አሊ እሁድ በሰጡት መግለጫ «ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ዙር የውሃ ሙሌት ብታካሂድም የሚደርሰን የውሃ መጠን የተረጋጋ ነው» ብለዋል፡፡
አትዮጵያ ግድቡን ለሁለተኛ ጊዜ መሙላት ብትችልም በግድቡ ሙሌት እና አስተዳደር ዙሪያ አሁንም ቢሆን አስገዳጅ ስምምነት መፈረም አለበት ብለዋል፡፡
ዳይሬክተሩ አል-ዴይም ጣቢያ ከሚያዚያ ወር ጀምሮ ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን የሚመጣውን የውሃ መጠን አለመቀነሱን አስታውቀዋል ሲል የኬኒያው የመገናኛ ብዙሃን ጋራዋ ኦንላይን አስነብቧል፡፡
ኢትዮጵያ ከተፋሰሱ ሀገራት ጋር አስገዳጅ ስምምነቶችን ለመፈረም እንደማትፈልግ በተደጋጋሚ አስታውቃለች።
አስገዳጅ ስምምነቶችን መፈረም የኢትዮጵያውያን የወደፊት የመልማት ፍላጎትን የሚገድብ ብቻ ሳይሆን ሉዓላዊነቷን የሚነካ ነው ብላ የምታምን መሆኑም ገልጻለች ፡፡
ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ሙሌት እንዲሁም በቴክኒክና በሕግ ጉዳዮች ዙሪያ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ለዓመታት ሲወያዩ ቆይተዋል፡፡
የግድቡ መጠናነቅ ከ60 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ዜጎች ኢትዮጵያውያን የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ ነው ፡፡